Smartፊደል ልጆች አማርኛን ወደውት እንዲማሩ ለልጆች በሚመጥን መልኩ በአስተማማኝነት የተዘጋጀ መማሪያ ነው። ይህ መማሪያ በተለይም ከ 3 እስከ 7 ዓመት ላሉ ልጆች የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ በእናቶች እና በባለሞያዎች ጥናት ተደርጎበት የተዘጋጀ ሲሆን፣ በደስታና በቀላል መንገድ እንዲማሩ የሚያደርግ ማስተማሪያ ነው።
ልጆች ከስክሪን ነጻ ሆነው በወረቀት እና በእርሳስ በመታገዝ የመናገር የመጻፍ የማዳመጥ እና የማንበብ ባህላቸውን ለማዳበር እና የቋንቋ ችሎታቸውን ለማሳደግ የተቀረፀ የአምስት ወራት ትምህርት ሲሆን ፣ አዳዲስ ፊደላትና አዳዲስ ትምህርቶችን የያዘ ሳምንቱን ልጆችዎ ሊለማመዱባቸውና ሊማሩባቸው የሚችሉባቸውን ከ70-80 ገጾችን የያዙ የመማሪያ መጻህፍት ጥራዞችን በተለይም በሰሜን አሜሪካ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ለ18 ሳምንት በየሳምንቱ በአድራሻዎ ቤትዎ ድረስ እንዲደርስ እናደርጋለን ።
በዚህ ፕሮግራም ፊደላትን በቅርጽ፣ በንድፍና በንባብ ማስተማሪያዎች ፣ በጽሁፍና በሰእል እንዲለማመዱ የሚያደርጉ እጅ ለማፍታቻ መለማመጃዎች፣ ለቅድመ ትምህርት የሚያዘጋጃቸው ከአካባቢያቸው የሚያውቁባቸው ሃሳቦች፣ የልጆች ታሪክ መጻህፍት፣ እና ሌሎችም ለልጆች መማሪያ የሚያገለግሉ ሃሳቦች የተካተቱበት የመጻህፍት ጥራዞች በየሳምንቱ እንልካለን።
የ Smartፊደል ማስተማሪያዎች የአንድ ወር የሙከራ እና የአምስት ወራት የሙሉ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። የአምስት ወራት ሙሉ ፓኬጅ ለሚገዙ የ 5% እንዲሁም በትምህርት ቤት፣ በቤተክርስትያን፣ በኮሚዩኒቲ ወይም በቤተሰብ ለሚመጡ ከ5 እና ከዚያ በላይ ሆነው በአንድ አድራሻ እንዲላክላቸው ለሚፈልጉ ቤተሰቦች የግሩፕ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። በዚህም ተጠቃሚ ለመሆን በGmail አካውንታችን smartfidel2025@gmail.com መልእክት ይጻፉልን እንዲሁም በስልክ ቁጥራችን ይደውሉ ውይም ቴክስት ያድርጉልን። በከፍተኛ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሆናሉ። ስለ አገልግሎታችን የሞከሩት ወላጆች ምስክሮቻችን ናቸው፣ ይሞክሩን በስራችን ውጤታማነትና በልጅዎ ለውጥ ተገርመው ለወዳጅዎ ይነግሩልናል።





Reviews
There are no reviews yet.